የፀጉር ቀለም መቀባት ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይጨምራል ተባለ

የፀጉር ውበትን ለመጠበቅ የሚያገለግሉ ቀለሞች ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድልን በከፍተኛ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርጉ አንድ ጥናት ጠቆመ። በአሜሪካ ሩትጀርስ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት ፀጉር ማጥቆሪያ ቀለም እና ማለስለሻ ኬሚካሎችን የሚጠቀሙ የተወሰኑ ሴቶች ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ሆኖ መገኘቱን አመላክቷል። ፀጉራቸውን ጥቁር ቀለም የሚቀቡ ጥቁር ሴቶች ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው 51 በመቶ ሲሆን፥ የፀጉር ማለስለሻ ቅባቶችን የሚጠቀሙ… Read More

በጀርባችን አና በጎናችን ላይ ያለን ትርፍ ስብ ለማስወገድ የሚረዱ ቀላል እንቅስቃሴዎች

ብዙውን ግዜ በጀርባችን አና በጎናችን ላይ ያሉ ስቦችን ስለማናያቸው ብቻ እንረሳቸዋለን:: ነገር ግን ይህ ትርፍ ስጋ አስቀያሚና አስቸጋሪ ሆኖ ይቀመጣል:: ለዚህም ነው እነኝህን ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎች  ለናንተ ይዘን የቀረብነው:: እነኝህን እንቅስቃሴዎች አዘውትረው ከሰሩ ከ2 እስከ 3 በሆነ ግዜ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ያያሉ:: ወደፊት መታጣፍ © DEPOSITPHOTOS ቀጥ ብለው እግርዎን በትከሻዎ ልክ አስፍተው ይቁሙ ጉልበትዎን ሳያጥፉ ወደፊት… Read More

ሎሚ ወይንም ለላ ነገር ሳንጠቀም እንዴት አድርገን ቆዳን ማፅዳትና ፈካ ያለ ማድረግ ይቻላል?

አሁን የምንነግራችሁ ውድህ በሁለት ደረጃ ነው የሚከናወነው። 1. መጀመርያ ማፅዳት የሚያስፈልጉ ንጥረ ነገሮች፡ ስኳር – 1 ማንኪያ የብርቱካን ጭማቂ – 1 ማንኪያ የኮኮናት ዘይት – 2 የሻይ ማንኪያ ማር – 2 የሻይ ማንኪያ ከላይ የተጠቀሱትን በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ አንድ ላይ በመደባለቅ በደንብ ይምቱት። ቢጫ ውህድ ያገኛሉ። ወፈር ባለ መልኩ ፊትዎን ከተቀቡ በኋላ ለ5 ደቂቃ ያክል… Read More

ጋቶች ፓኖም ለአንዚ ማካቻካላ ፈረመ

ኢትዮጵያዊው አማካይ ጋቶች ፓኖም ለሩስያው ክለብ አንዚ ማካቻካላ ለመጫወት ትናንት ፊርማውን አኖሯል፡፡ የተጫዋቹ ወኪል ዴቪድ በሻ እንደገለፀው፥ ጋቶች ለሶስት ዓመት ለማካቻካላ ከተማው ክለብ ለመጫወት ተስማምቷል። ጋቶች ከሳምንት በፊት ወደ ሩስያ አቅንቶ የሙከራ ጊዜ እያሳለፈ ይገኝ የነበረ ሲሆን የሙከራ ጊዜው የአንዚ ክለብ አሰልጣኞችን ያስደሰተ በመሆኑ ተጫዋቹን ለማስፈረም በቅተዋል። የክለቡ ፕሬዚደንት በፊፋ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሃገራቸው ሩስያ ከኒውዝላንድ… Read More

ከቃሪያ የተሰራው የህመም ማስታገሻ መድሃኒት…

ቃሪያ የተለያዩ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት በተለያዩ ጊዜያት የወጡ ጥናቶች አመላክተዋል። አሁን ደግሞ ከቃሪያ የተቀመመ የህመም ማስታገሻ መድሃኒት የጉልበት ህመምን በማስታገስ ረገድ ውጤታማ መሆኑ ነው የተነገረው። ቃሪያ ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገርን ከቃሪያ ተክል ላይ በመምጠጥ የተዘጋጀው መድሃኒት “ኦስቴኦርተሪቲስ” የተባለ የእግር ጉልበት መገጣጠሚያ ህመምን እስከ 6 ወር ማስታገስ እንደሚችል ተነግሯል። ህመም ባለበት ስፍራ በመርፌ በመውጋት የሚሰጠው ይህ… Read More

ተገቢ ያልሆኑ የሰራተኛ አያያዞች ሰራተኞች ህግጋትን እንዳያከብሩ ይገፋፋሉ – ጥናት

በስራ ገበታቸው ላይ መልካም ያልሆነ አያያዝ የሚገጥማቸውና በግለሰቦች ስሜታዊ ውሳኔ የሚጎዱ ሰዎች ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር መልካም ግንኙነት አይኖራቸውም። ይህም በስራ ቦታ ያጋጠሙ አሉታዊ ጫናዎችን በማስታወስ፥ በቤት ውስጥ ለልጆች፣ ለትዳር አጋር አልያም ለሌላ የቤተሰብ አባል መልካም እይታ እንዳይኖራቸው ያደርጋል፡፡ ጠንካራ ሰራተኞች በከፍተኛ የስራ ጫና እንዲሁም ባልተገቡ ውሳኔዎች ውስጥ የስራ ቀናቸውን የሚያሳልፉ ከሆነ፥ በቤተሰባቸው… Read More

ጎግል ሽብርን በሚያራምዱ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለውን እቅድ ይፋ አደረገ

ጎግል ሽብርን የሚያራምዱ የዩቲዩብ ቪዲዮዎችን ለመከላከል የሚያስችለውን ዝርዝር እቅድ ይፋ አድርጓል:: የሽብር አቋምን የሚያንጸባርቁ ቪዲዮዎች ማህበረሰቡ በፍርሃትና በስጋት በተሞላበት አኗኗር እንዲኖር የሚያስገድድ ስነልቦናዊ ጫና ይፈጥራሉ፡፡ አንዳንድ ሀገራት ሽብርን ለመዋጋት የሚያደርጉት ጥር ቢኖርም ብቻቸውን ስኬታማ ስራ ሊሰሩ ስለማይችሉ፥የግሉ ዘርፍም ሽብርን በመዋጋት ረገድ የራሱን ሚና ሊጫወት እንደሚገባ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ ለአብነትም ጎግል በዩቲዩብ ኩባንያው በኩል ሽብርን ለመከላከል የሚያደርገው… Read More

ሳዑዲ ያወጣችው የምህረት አዋጅ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ቢቀሩትም የተመላሾች ቁጥር ግን አናሳ ነው

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የስራና የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎች ከሀገሪቱ እንዲወጡ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ 10 ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ያነጋገራቸው ከሳዑዲ ተመላሾች የምህረት አዋጁ ሳይጠናቀቅ በመምጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን፥ ቀነ ገደቡ እስከሚያልቅ ቢቆዩ ግን ሊደርስ የሚችለው አስከፊ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ዜጎች እንግልት ሳይደርስባቸው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ብሄራዊ… Read More

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሰኔ ወር መጨረሻ ለባለዕድለኞች ይተላለፋሉ- ሚኒስቴሩ

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሰኔ ወር መጨረሻ ለባለዕድለኞች በዕጣ እንደሚተላለፉ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ ዶክተር አምባቸው መኮንን ገለፁ። ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ የመስሪያ ቤታቸውን የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ነው። ዶክተር አምባቸው ቤቶቹን በዕጣ ለማስተላለፍ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ተናግረዋል። የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ከኢትዮጵያ ንግድ… Read More

ኢትዮጵያ የኢ-ቪዛ አገልግሎት ጀመረች

ከተለያዩ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በኢንተርኔት መመዝገብ የሚችሉበት አሰራር ተግባራዊ ተደረገ። አሰራሩ ከተለያዩ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ሳይጉላሉ፥ በቀጥታ በኢንተርኔት በመመዝገብ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች መምሪያ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድም አሰራሩን በጥምረት ማዘጋጀታቸውን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተገኘው መረጃ ያሳያል። በዚህ መሰረት መንገደኞች ወደ ኢትዮጵያ መግባት ሲፈልጉ፥ ባሉበት ቦታ… Read More